The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Chargers [Al-Adiyat] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The Chargers [Al-Adiyat] Ayah 11 Location Maccah Number 100
1. እያለከለኩ ሩዋጮች በሆኑ (ፈረሶች)፤
2. ምድርን በሸሆናቸው እያጋጩ የእሳት ብልጭታን አውጪዎች በሆኑትም (ፈረሶች)፤
3. በማለዳ (በጧት) ወራሪዎች በሆኑትም ፈረሶች፤
4. በእርሱም አቧራን በቀሰቀሱት፤
5.በፈረሰኞቻቸው በኩል (የጠላት) ስብስብ መሀልን በተጋፈጡትም (ፈረሶች) እምላለሁ።
6. የሰው ልጅ ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው::
7. እርሱም በዚያ ክህደቱ ላይ መስካሪ ነው::
8. እርሱም ገንዘብን በመውደድ ላይ በጣም ብርቱ ነው::
9. የሰው ልጅ በመቃብሮች ዉስጥ ያሉት ሙታን ሁሉ በተቀሰቀሱ ጊዜ ምን እንደሚከሰት አያውቅምን?
10. በልቦች ውስጥ ያለዉም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ እንዴት እንደሚሆን አያውቅምን?
11. ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ ነገር በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው::