The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Calamity [Al-Qaria] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The Calamity [Al-Qaria] Ayah 11 Location Maccah Number 101
1. ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤
2. ቆርቋሪይቱ (ጩኸት) ምንድን ናት!
3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቆርቋሪይቱ ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?
4. ሰዎች እንደተበታተነ ቢራቢሮ (ኩብኩባ) የሚሆኑበት ቀን፤
5. ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ የሚሆኑበት (አስደንጋጭ ቀን) ናት።
6. በዚያ ዕለት ያ ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ
7. እርሱ ኑሮው በአሰደሳቿ ጀነት ውስጥ ይሆናል።
8. ያ ሚዛኖቹ የቀለሉበት ሰው ደግሞ
9. መኖሪያው ሃዊያህ (የምትባል የገሀነም እሳት) ናት።
10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሷ ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?
11. (እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት::