The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesCompetition [At-Takathur] - Amharic translation - Africa Academy
Surah Competition [At-Takathur] Ayah 8 Location Maccah Number 102
1. (በዚህች ዓለም ጸጋዎች) ብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘናጋችሁ::
2. መቃብሮችን እስከጎበኛችሁ ድረስ:: (በዚሁ ላይ ቀጠላችሁ)።
3. ከዚህ ተግባራችሁ ተከልከሉ (ታቀቡ):: ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፤
4. ከዚያም ከዚህ ተግባራችሁ ተከልከሉ። ወደ ፊትም ታውቃላችሁ፤
5. በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) በእርግጠኝነት ብታውቁ ኖሮ (ይህን ያክል ባልተዘናጋችሁ ነበር)።
6. ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ::
7. ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፤
8. ከዚያም በድሎታችሁ ጉዳይ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃለችሁ::