The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Traducer [Al-Humaza] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The Traducer [Al-Humaza] Ayah 9 Location Maccah Number 104
1. ለሐሜተኛ፤ ለዘላፊ፤ (ለአሽሟጣጭ ሁሉ) ወዮለት::
2. ለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበዉም) ለሆነ ሁሉ፡፡
3. ገንዘቡ በዚህች ዓለም ዘውታሪ እንደሚያደርገው ያስባል።
4. በጭራሽ፤ አውዳሚና የምትፈጭ በሆነችው እሳት ውስጥ በእርግጥ ይጣላል።
5. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምትፈጨዋም ምን እንደሆነች ምን አሳወቀህ?
6. የተቀጣጠለችው የአላህ እሳት ናት::
7. ያቺ በልቦች ላይ እንኳን ሳይቀር የምትዘልቅ የሆነች::
8. እርሷ በእርግጥ በእነርሱ ላይ የተዘጋች ናት::
9. በተዘረጋች አዕማድ ውስጥ የተዘጋች ናት::