The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe moon [Al-Qamar] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The moon [Al-Qamar] Ayah 55 Location Maccah Number 54
1. የትንሳኤ ቀን ተቃረበ:: ጨረቃም ተገመሰ::
2. ከሓዲያን ተዐምርን ቢያዩም እንቢ ብለው ይዞራሉ:: «ይህ ዘውታሪ ድግምት ነው» ይላሉ::
3.አስተባበሉም :: ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ:: ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው) ረጊ ነው።
4. ከዜናዎቹ በእርሱ ውስጥ መገሰጫ የሚሆን ነገር ያለበት በእርግጥ መጣላቸው::
5. ሙሉ ከሆነ ጥበብ (መጣላቸው):: ግን አስፈራሪዎች (ለማያምኑት) አይፈይዱም።
6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ተውና ዙር። (ይልቁንስ) ጠሪው መልዓክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ።
7. ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ሆነውና ፍጹም የተበተኑ አንበጣ መስለው ከየመቃብሮቻቸው ይወጣሉ::
8. ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎችና ቸኳዩች ሆነው ይወጣሉ:: ከሓዲያን ያን ጊዜ «ይህ ብርቱ ቀን ነው» ይላሉ።
9. ከእነርሱ በፊት የ(ነብዩ) ኑህ ህዝቦች አስተባበሉ:: ባሪያችንንም ኑህን አስተባበሉ:: «ዕብድ ነዉም» አሉት:: ተገላመጠም::
10. «ጌታውንም እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ተጣራ::
11. ወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን::
12. የምድርንም ምንጮች በሃይል አፈነዳን:: የሰማዩና የምድሩ ውሃዉም ቀድሞ በተወሰነ ሁኔታ ላይ ተገናኘ::
13. ባለ ብዙ ሳንቃዎችና ባለ ብዙ ሚስማሮች በሆነቸው ታንኳ ላይም ጫንነው::
14. በጥበቃችን ስር ሆና ትንሻለላለች፡፡ ተክዶ ለነበረ ሰው ምንዳ ይህን ሰራን።
15. ተዓምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት:: ተገሳጭ አለን?
16. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?
17. ቁርኣንን ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው:: ተገንዛቢ አለን?
18. የዓድ ህዝቦች አስተባበሉ:: ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ፤
19. እኛ በእነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በሆነ ቀን በኃይል የምንትሻሻ ነፋስን ላክንባቸው::
20. ሰዎችንም ልክ ከስሮቻቸው እንደተጎለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው ከየተደበቁበት ትነቅላቸዋለች::
21. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?
22. ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው:: ተገሳጭ አለን?
23. የሰሙድ ህዝቦች በአስፈራሪዎቹ አስተባበሉ::
24. (እንዲህም) አሉ: «ከእኛ የሆነን አንድን ሰው እንከተለዋለን? እኛ ያ! ጊዜ በስህተትና በእብደት ውስጥ ነን አሉ።
25. «ከእኛ መካከል በእርሱ ላይ ብቻ ማስገንዘቢያ ራዕይ ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ውሸታም ኩሩ ነው» አሉ::
26. ውሸታሙ ኩሩው ማን እንደሆነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ::
27. እኛ ሴት ግመልን ለእነርሱ መፈተኛ ትሆን ዘንድ ላኪዎች ነን:: ተጠባበቃቸዉም ታገስም::
28. ውሃዉም በመካከላቸው የተከፈለ መሆኑን ንገራቸው:: ከውሃ የሆነ ፈንታ ሁሉ በየተራ የሚጣዱት ነው።
29. ጓደኛቸውንም ጠሩት:: ወዲያዉም (ሰይፉን) ተቀበለ:: ወጋትም::
30. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?
31. እኛ በእነርሱ ላይ አንዲትን ጩኸት ላክንባቸው። ወዲያዉም ከበረት አጣሪ (አጥር) እንደ ተሰባበረ እርጋፊ ሆኑ።
32. ቁርኣንን ለመገንዘብ አገራነው:: ተገሳጭ አለን?
33. የ(ነብዩ) ሉጥ ህዝብ በአስፈራሪዎቹ አስተባበሉ::
34. እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስ ላክን:: የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱንስ በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው::
35. ከእኛ በሆነ ጸጋ አዳናቸው:: ልክ እንደዚሁ ያመሰገነን ሰው እንመነዳለን::
36. ብርቱ አያያዛችንን በእርግጥ አስጠነቀቅናቸው:: በማስጠንቀቂያዎቹም ተከራከሩ።
37. ከእንግዶቹም እንዲያስመቻቸው ደጋግመው ፈለጉት። ወዲያዉም ዓይኖቻቸውን አበስን። ቅጣቱንና ማስጠንቀቂያዎቹን ቅመሱ አልናቸው።
38. በማለዳም ዘወታሪ የሆነ ቅጣት በእርግጥ ማለደባቸው::
39. ቅጣቱንና ማስጠንቀቂያዎችም ቅመሱ ተባሉ::
40 ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው:: ተገሳጭ አለን?
41.የፈርዖንን ቤተሰቦችም ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጧቸው።
42. በተዓምራታችንም በሁሏም አስተባበሉ:: የብርቱ ቻይንም አቀጣጥ ቀጣናቸው::
43. የእናንተ ከሓዲያኖቻችሁ ከእነዚያችሁ በላጮች ናቸውን? ወይስ ለእናንተ በመጽሐፎች ውስጥ በተለየ የተነገረ ነፃነት አላችሁ?
44. ወይስ «እኛ የተረዳን ክምቹዎች ነን» ይላሉ?
45. ክምቹዎቹ በእርግጥ ድል ይመታሉ:: ጀርባዎቻቸውንም ያዞራሉ::
46. ይልቁንም ሰዓቲቱ ትንሳኤ ቀጠሯቸው ናት:: ሰዓቲቱም በጣም የከበደችና የመረረች ናት::
47. አመጸኞች በስህተትና በእሳቶች ውስጥ ናቸው::
48. በእሳት ውስጥ በፊታቸው በሚጎተቱበት ቀን የሰቀርን (የገሀነምን) ቅጣት መንካትን ቅመሱ ይባላሉ::
49. እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው::
50. ትዕዛዛችንም እንደ ዓይን ቅጽበት የሆነች አንዲት ቃል እንጂ ሌላ አይደለችም::
51. ብጤዎቻችሁንም በእርግጥ አጠፋን፤ ተገሳጭ አለን?
52. የሰሩትም ነገር ሁሉ በመጽሐፎች ውስጥ ነው::
53. ትንሹም ትልቁም ሁሉ የተፃፈ ነው::
54. አላህን ፈሪ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በአትክልቶችና በወንዞች ውስጥ ናቸው::
55. እነርሱም (ውድቅ ቃልና መውወንጀል በሌለበት) በእውነት መቀመጫ ውስጥ ላይ ከሆነው ንጉስ አላህ ዘንድ ናቸው::