The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesMutual Disillusion [At-Taghabun] - Amharic translation - Africa Academy
Surah Mutual Disillusion [At-Taghabun] Ayah 18 Location Madanah Number 64
1. በሰማያት ውስጥም ሆነ በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ አላህን ያሞግሳል:: ንግስናው የእርሱ ብቻ ነው:: ምስጋናም ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው::
2. እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው:: ከእናንተም መካከል ከሓዲ አለ:: ከእናተም መካከል አማኝ አለ:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነው::
3. (እርሱ) ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ:: ቀረጻችሁም ቅርጻችሁንም አሳመረ፡፡ መመለሻችሁም ወደ እርሱ ብቻ ነው::
4. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: የምትደብቋትንም ሆነ የምትገልጡትን ያውቃል:: አላህም በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
5. የእነዚያ ከአሁን በፊት የካዱትና የክህደታቸውን ቅጣት የቀመሱ ህዝቦች ወሬ አልመጣላችሁምን? ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::
6. ይህ (ቅጣት) እነርሱ መልዕክተኞቻቸው አስረጂዎችን ይዘው ሲመጡላቸው «ሰዎች ይመሩናልን?» ስላሉና ስለ ካዱ፤ ከእምነትም ስለ ዞሩ ነው:: አላህ ከእነርሱ እምነት ተብቃቃ:: አላህ ተብቃቂና ምስጉን ነውና::
7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች በፍጹም የማይቀሰቀሱ መሆናቸውን አሰቡ። «(እንዴት አትቀሰቀሱም?) በጌታየ ይሁንብኝ ትቀሰቀሳላችሁ:: ከዚያ ትፈጽሙት የነበረውን ተግባራችሁን ትናገራላችሁ:: ይህ ተግባር ለአላህ ቀላል ነው» በላቸው።
8. በአላህ በመልዕክተኛውና በዚያም ባወረድነው ብርሃን እመኑም:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና።
9. (ይኸዉም) ለመሰብሰቢያው ቀን የሚሰበስባችሁ እለት አስታውሱ:: ይህ ቀን የቁጭት ቀን ነው:: በአላህም የሚያምን ሰው መልካምንም የሚሠራ ከርሱ ኃጢአቶቹን ይሰርይለታል፤ (ይፍቅለታል)፤ ከስሮቿ ወንዞች የሚፈሱባት ገነቶች ለዘላለም ያስገባዋል:: ይህ ታላቅ እደለኝነት ነው::
10. እነዚያም የካዱትና በአንቀፆቻችንም ያስተባበሉት የዝንታለም እሳት ባለቤቶች ማለት እነርሱ ናቸው:: (ጀሀነም) መመለሻነቷ ምን ይከፋ!
11. ከመከራም በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ ማንንም አይነካም:: በአላህ የሚያምን ሰው አላህ ልቡን ለትግስት ይመራዋል:: አላህም በሁሉም ነገር አዋቂ ነው::
12. አላህን ታዘዙ መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: ብትዞሩም (መልዕክተኛውን አትጎዱም::) በመልዕክተኛችንም ላይ ያለበት በግልጽ ማድረስ ብቻ ነው::
13. አላህ ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላክ የለም:: ትክክለኛ አማኞች በአላህ ብቻ ይመኩ::
14. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሚስቶቻችሁና ከልጆቻችሁ (ከአላህ መንገድ በማስተጓጎል) ለእናንተ ጠላቶች የሆኑ አሉ:: ስለዚህ ተጠንቀቋቸው:: ይቅርታ ብታደርጉ፤ ብታልፏቸዉም፤ ብትምሩዋቸዉም፤ አላህ በጣም መሀሪ፤ አዛኝ ነው::
15. ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለእናንተ መፈተኛ ብቻ ናቸው:: አላህም ከእርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አለ::
16. አላህንም የቻላችሁትን ያህል ፍሩት:: ትዕዛዙን ስሙም፤ ታዘዙም፤ ለግሱም፤ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ይሰጣችኋልና:: የነፍሶቻቸዉን ንፍገት የሚጠበቁ ሰዎች ሁሉ እነዚያ እነርሱ ፍላጎታቸውን የሚያገኙ ናቸው::
17. ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩት (ምንዳውን) ለእናንተ ይደራርበዋል:: ለእናንተም ይምራል:: አላህ አመስጋኝና ታጋሽ ነውና::
18. (እርሱ) ስውሩንም ይፋዉንም ሁሉን አዋቂ ኃያልና ጥበበኛ ነዉና።