The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe enshrouded one [Al-Muzzammil] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The enshrouded one [Al-Muzzammil] Ayah 20 Location Maccah Number 73
1. አንተ ተከናናቢው ሆይ::
2. ሌሊቱን (ሁሉ) ጥቂት ሲቀር ቁም (ስገድ)::
3. ግማሹን (ቁም) ወይም ከእርሱ ጥቂትን ቀንስ::
4. ወይም በእርሱ ላይ ጨምር:: ቁርኣንንም በዝግታ አንብብ::
5. እኛ ባንተ ላይ ከባድ ቃልን እናወርዳለንና::
6. ሌሊት መነሳት (ህዋሳትንና ልብን) ለማስማማት በጣም ብርቱ ነው:: ለማንበብም ትክክለኛ ሰዓት ነው::
7. ላንተ በቀን ውስጥ ረዥም የመዘዋወርያ ሰዓት አለህ::
8. የጌታህን ስም አውሳ:: ወደ እርሱም (አምልኮ) መቋረጥን ተቋረጥ::
9. (እርሱም) የምስራቅና የምዕራብ ጌታ ነው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: መጠጊያ አድርገህም ያዘው::
10. (ከሓዲያንም) በሚሉት ላይ ታገስ:: መልካምንም መተው ተዋቸው::
11. የድሎት ባለቤቶችም ከሆኑት አስተባባዮች ጋር ተወኝ:: ጥቂትንም ጊዜ አቆያቸው::
12. ከእኛ ዘንድ ከባድ ማሰሪያዎችና እሳት አሉንና::
13. (ጉሮሮን) የሚያንቅ ምግብና አሳማሚ ቅጣትም አለ።
14. በዚያ ምድርና ጋራዎች በሚርገፈገፉበት፤ ጋራዎችም ፈሳሽ የአሸዋ ክምር በሚሆኑበት ቀን::
15. እኛ ወደ ፊርዖን መልዕክተኛን እንደላክን ሁሉ በእናንተ ላይ መስካሪ መልዕክተኛንም ወደ እናንተ ላክን።
16. ፊርዓውንም መልዕክተኛውን አመጸ:: ብርቱ መያዝንም ያዝነው::
17. (በአላህ) ከካዳችሁ ያን ልጆችን ሸበቶዎች የሚያደርገውን ቀን ቅጣት እንዴት ትጠነቀቃላችሁ?
18. ሰማዩ በቀኑ ተሰንጣቂ ነው:: ቀጠሮዉም ተፈፃሚ ነው::
19. ይህች መገሰጫ ናት። መዳንንም የሻ (የፈለገ) ሰው ወደ ጌታው (የሚያደርሰዉን) መንገድ ይይዛል::
20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ከሌሊቱ ሁለት እጅ ያነሰን፤ ግማሹንም ሲሶውንም የምትቆም መሆንህን ጌታህ ያውቃል:: (ሙስሊሞች) ከእነዚያም አብረውህ ካሉ ከፊሎች የሚቆሙ መሆናቸውንም ያውቃል:: አላህ ሌሊትና ቀንን ይለካል:: ሌሊቱን በሙሉ የማትቆሙት መሆናችሁን አወቀ:: እናም በእናንተ ላይ ህጉን ወደ ማቃለል ተመለሰላችሁ:: ስለዚህ ከቁርኣን (በስግደት) የተቻላችሁን ያህል አንብቡ:: ከናንተ ውስጥ ሌሎችም በሽተኞች ከአላህ ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ የሚጓዙ ሌሎችም፤ በአላህ መንገድ ሃይማኖት ላይ የሚጋደሉ እንደሚኖሩ አወቀ:: አቃለለላቸዉም ከቁርኣን የቻላችሁትን አንብቡ:: ሶላትንም ስገዱ:: ዘካንም ስጡ:: ለአላህ መልካም ብድርንም አበድሩ:: ከመልካም ስራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ሆኖ በአላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ:: አላህን ምህረት ለምኑት:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::