عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The man [Al-Insan] - Amharic translation - Africa Academy

Surah The man [Al-Insan] Ayah 31 Location Madanah Number 76

1. በሰው ላይ የሚታወስ ነገር (እንኳ) ሳይሆን ከዘመናት የተወሰነ ጊዜ አላለፈም ነበርን? (በእርግጥ አልፏል)።

2. እኛ ሰውን (በሕግጋት ግዳጅ) የምንሞክረው ስንሆን ከወንድና ከሴት ፈሳሽ ቅልቅሎች ከሆነች የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው:: ሰሚና ተመልካችም አደረግነው።

3. እኛ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲሆን መንገዱን መራነው::

4. እኛ ለከሓዲያን ሰንሰሎቶችንና እንዛዝላዎችን፣ እሳትንም (አዘጋጅተናል)::

5. እነዚያ (ትክክለኛ) በጎ አድራጊዎች መበረዣዋ ካፉር ከሆነች ጠጅ ይጠጣሉ::

6. ከእርሷ እነዚያ የአላህ ባሮች የሚጠጡላት ና ወደ ፈለጉበት ማንቧቧትን የሚያንቧቧት ከሆነች የጠጅ ምንጭ (ይጠጣሉ)::

7. (ዛሬ በዚህ ዓለም እያሉ) በስለታቸው ይሞላሉ:: መከራው ተሰራጪ የሆነንም ቀን ይፈራሉ::

8. ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድሃ፤ ለየቲምና ለምርኮኛ ያበላሉ::

9. «የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው:: ከናንተ ክፍያንም ሆነ ማመስገንን አንፈልግም::

10. እኛ ያንን (ፊትን) የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና» (ይላሉ)።

11. አላህም የዚያን ቀን ክፋት ጠበቃቸው። (ፊታቸው) ማማርንና መደሰትንም ገጠማቸው::

12. በመታገሳቸዉም (ምክንያት) ገነትንና የሀር ልብስን መነዳቸው::

13. በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች፤ በውስጧ የጸሀይን ሐሩርንም ሆነ ብርድንም የማያዩ ሲሆኑ፤

14. ዛፎቿም ለእነርሱ የቀረበች፤ ፍራፍሬዎችዋም ለለቃሚዎች መገራትን የተገራች ስትሆን ገነትን መነዳቸው::

15. በእነርሱም ላይ ከብር በተሰሩ ዕቃዎች (ሳህኖች)፤ ብርጭቆዎች እና በኩባያዎችም ይዝዞርባቸዋል::

16. መለካትን የለኳቸው በሆኑ የብር ብርጭቆዎች (ይዝዞርባቸዋል)::

17. በእርሷም መበረዣዋ ዝንጂብል የሆነች ወይን ጠጅ ይጥጠጣሉ።

18. በውስጧ ያለችውን ሰልሰቢል ተብላ የምትጠራውን ምንጭ::

19. በእነርሱም ላይ ባሉበት ሁኔታ የሚዘወትሩ ወጣት ልጆች ይዘዋወራሉ:: ባየሃቸው ጊዜ የተበተነ ሉል ናቸው ብለህ ታስባቸዋለህ::

20. እዚያንም በተመለከትክ ጊዜ ጸጋንና ታላቅ ንግስናን ታያለህ::

21. አረንጓዴዎች የሆኑ ቀጭን ሀር ልብሶችና ወፍራም ሀርም በላያቸው ላይ አለ። ከብር የሆኑ አንባሮችንም ይሸለማሉ:: ጌታቸዉም (ከራሱ አልፎ) ሌላን አጥሪ የሆነን መጠጥ ያጠጣቸዋል::

22. «ይህ ለእናንተ ዋጋ ሆነ:: ስራችሁም ምስጉን ሆነ» ይባላሉ::

23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ (ይህንን) ቁርኣን ባንተ ላይ ማውረድን አወረድነው።

24. ለጌታህ ፍርድም ታገስ:: ከእነርሱም መካከል ኃጢአተኛን ወይም ከሓዲን አትታዘዝ::

25. የጌታህን ስም በጠዋትና ከቀትር በኋላ አውሳ::

26 ከሌሊቱም ለእርሱ ብቻ ስገድ፤ በረዢም ሌሊትም አወድሰው።

27. እነዚያ ይህችን ፈጣኒቱን ዓለም ይወዳሉ። ከባድና (አስቸጋሪ) ቀንም በስተፊታቸው ሆኖ ችላ ይላሉ::

28. እኛ ፈጠርናቸው:: የአካሎቻቸዉንም መለያያቸውን አጠነከርን:: በፈለግን ጊዜ መሰሎቻቸውን መለወጥን እንለውጣለን።

29. ይህ መገሰጫ ነው:: የፈለገ ሰውም ወደ ጌታው መንገድ ይይዛል::

31. (አላህ) የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባዋል:: በዳዩችንም (ዝቶባቸዋል) ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅቶላቸዋል::