عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The Cleaving [AL-Infitar] - Amharic translation - Africa Academy

Surah The Cleaving [AL-Infitar] Ayah 19 Location Maccah Number 82

1. ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤

2. ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤

3. ባህሮችም በተከፈቱና በተደባለቁ ጊዜ፤

4. መቃብሮችም በተገለባበጡና ሙታን በተነሱ ጊዜ፤

5. (ያኔ) ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያዘገየችውን ታውቃለች።

7. በዚያ በፈጠረህ፤ አካለ ሙሉም ባደረገህ፤ ባስተካከለህም፤

8. በማንኛውም (እርሱ) በፈለገው ቅርጽ በገጣጠመህ ጌታህ ምን አታለለህ?

9 (ሰዎች ሆይ!) ተከልከሉ፤ በእውነት በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ።

10. በእናንተ ላይ ጠባቂዎች ያሉባችሁ ስትሆኑ፤

11. የተከበሩ ጸሐፊዎች የሆኑ (ተጠባባቂዎች)፤

12. የምትሰሩትን (ሁሉ) ያውቃሉ፤

13. (እውነተኞቹ) ደጋጎች በእርግጥም በገነት ውስጥ ናቸው።

14.ከሓዲያንም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው::

16.እነርሱም (ምን ጊዜም) ከእርሷ ራቂዎች አይደሉም::

17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የፍርዱ ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

18. ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደሆነ ምን አሳወቅህ?

19. (እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግ የማትችልበት ቀን ነው:: ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው::