The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Mansions of the stars [Al-Burooj] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The Mansions of the stars [Al-Burooj] Ayah 22 Location Maccah Number 85
1. የህብረ ከዋክብት ባለቤት በሆነችው ሰማይ፤
2. በተቀጠረዉም ቀን፤
3. በመስካሪና በሚመሰከርበትም እምላለሁ::
4. የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ::
5. የባለማገዶዋ እሳት ባለቤቶች።
6. እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በሆኑ ጊዜ (ተረገሙ)።
7. እነርሱም በምዕመኖች ላይ ለሚሰሩት (ማሰቃየት) መስካሪዎች ናቸው።
8. ከእነርሱም በአሸናፊውና በምስጉኑ ጌታ ማመናቸውን እንጂ ሌላን ምንንም አልጠሉም::
9. ያ የሰማይና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነውን (ነው ያመኑበት)። አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው (አዋቂ ነው)።
10. እነዚያ አማኞችና ምዕመናትን ያሰቃዩና ከዚያ ያልተጸጸቱ ሁሉ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አለላቸው:: ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው::
11. እነዚያ በአላህ አምነው መልካም ስራዎችን የሰሩ ሁሉ ለእነርሱ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው:: ይህ ታላቅ ስኬት ነው::
12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ በኃይል መያዝ ብርቱ ነው።
13. እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም::
14. እርሱም ምህረቱ የበዛ ወዳድ ነው::
15. የላቀው የዙፋኑ ባለቤት ነው።
16. የሚሻውን ሁሉ ሰሪ (ፈፃሚ) ነው::
17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! የእነዚያ ነብያትን ያስተባበሉ) ሰራዊቶች ወሬ መጣልህን?
18. የፊርዓውንና የሰሙድ (ወሬ ደርሶሃልን)?
19. በእውነት እነዚያ (በአላህ) የካዱት (ሰዎች ሁሉ) እውነትን በማስተባበል ውስጥ ናቸው::
20. አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው::
21. ይልቁንም እርሱ የተከበረ ቁርኣን ነው::
22. የተጠበቀ በሆነ ሰሌዳ (ሎህ) ውስጥ ነው::