The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe morning star [At-Tariq] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The morning star [At-Tariq] Ayah 17 Location Maccah Number 86
1. በሰማዩ እና ሌሊት በሚመጣውም እምላለሁ።
2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሌሊት መጪው ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?
3. ጨለማውን ሰንጣቂ ኮከብ ነው::
4. ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጂ ሌላ አይደለችም::
5. የሰው ልጅ ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፤
6. ከተስፈንጣሪ ውሃ (የዘር ፈሳሽ) ተፈጠረ::
7. ከጀርባና ከእርግብግቢቶች መካከል የሚወጣ ከሆነ የዘር ፈሳሽ ውሃ (ተፈጠረ)።
8. አላህ እርሱን በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው::
9. ሚስጥሮች በሚገለጹበት ቀን፤
10. (ለሰው) ምንም ኃይልና ረዳት አይኖረዉም::
11. የመመለስ ባለቤት (ዝናባማ) በሆነችው ሰማይ እምላለሁ::
12. (በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በሆነችው ምድርም እምላለሁ::
13. እርሱ (ቁርኣን)፤ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ (የአላህ) ቃል ነው።
14. እርሱም ቀልድ አይደለም።
15. እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ያሴራሉ (ይሸርባሉ)::
16. እኔ ተንኮልንም እመልሳለሁ (አመክናለሁ)::
17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያንን ቀን ሰጣቸው:: ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው (ታገሳቸው)::