The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Overwhelming [Al-Ghashiya] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The Overwhelming [Al-Ghashiya] Ayah 26 Location Maccah Number 88
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሸፋኝቱ ትንሳኤ ወሬ መጣልህን?
2. በዚያ ቀን የከሓዲያን ፊቶች ተዋራጆች ናቸው::
3. ሰሪዎች ለፊዎች ናቸው::
4. የምታቃጥልን እሳት ይገባሉ::
5. በጣም ከፈላች ምንጭም ይጋታሉ::
6. ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃማ) ዛፍ እንጂ ሌላ ምግብ የላቸዉም::
7. አካልን አያሰባ፤ ከረኃብም አያብቃቃ፤
8. (የአማንያን) ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው::
9. በስራቸውም ተደሳቾች ናቸው::
10. በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው::
11. በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም::
12. በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አሉ::
13. በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አሉ::
14. በተርታ የተኖሩ ኩባያዎችም፤
15. የተደረደሩ መከዳዎችም፤
16. የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አሉ)::
17. (ከሓዲያን) ግመል እንዴት እንደተፈጠረች አይመለከቱምን?
18. ሰማይም እንዴት ከፍ እንደተደረገች!
19. ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!
20. ምድርም እንዴት እንደተዘረጋች አይመለከቱምን?!
21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስታውስም:: አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና::
22. በእነርሱ ላይ አስገዳጅ (ተሿሚ) አይደለህም፤
23. ግን ከእውነት የዞረና የካደ፤
24. አላህም ከባዱን ቅጣት ይቀጣዋል።
25. መመለሻቸው ወደ እኛ ብቻ ነው::
26. ምርመራቸዉም በእኛ ላይ ብቻ ነው::