عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The City [Al-Balad] - Amharic translation - Africa Academy

Surah The City [Al-Balad] Ayah 20 Location Maccah Number 90

1. በዚህ ሀገር (በመካ) እምላለሁ

2.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትሆን።

3.በወላጂና በወለዳቸውም (በአደምና በዘሮቹ) ሁሉ (እምላለሁ)።

4. ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ሆኖ ፈጠርነው::

5. በእርሱ ላይ አንድም አካል የማይችል መሆኑን ይጠረጥራልን?

6. "ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ" ይላል፤

7. አንድም ያላየው መሆኑን ያስባልን?

8. ለእርሱ ሁለት አይኖችን አላደረግንለትንምን?

9. አንድ ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፤

10.ሁለትን መንገዶችስ አልመራነዉምን?

12.ዐቀበቱን መውጣት ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?

13.ያ ጫንቃን መልቀቅ ነው። {1}

14. ወይም የረሀብ ባለቤት በሆነ ቀን (ረሀብተኛን) ማብላት፤

15. የዝምድና ባለቤት የሆነን የቲም፤

16.ወይም የአፈር ባለቤት የሆነን (ችግረኛ) ማብላት ነው።

17.ከዚያም ከእነዚያ በአላህ ካመኑትና በመታገስ ላይ አደራ ከተባባሉት ሰዎች ጋር መሆን ነው።

18. እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው።

19. እነዚያ በአናቅጻችን የካዱ ሁሉ እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው።

20. ለእነርሱ የምትዘጋባቸው እሳትም አለች።