The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe night [Al-Lail] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The night [Al-Lail] Ayah 21 Location Maccah Number 92
1. በሌሊቱ (ጨለማውን) በሚሸፍነው ጊዜ፤ (እምላለሁ)
2. በቀኑም በተገለጸ ጊዜ፤
3. ወንድንና ሴትን በፈጠረዉም (አምላክ) እምላለሁ::
4. ስራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው።
5. ያ! የሰጠና ጌታውንም የፈራማ፤
6. በመልካሚቱ እምነትም ያረጋገጠ ሰው
7. ለገሪቱ እናገራዋለን።
8. ያ! የሰሰተ በራሱም የተብቃቃ፤
9. በመልካሚቱም ያስተባበለውማ
10. ለክፋት እናዘጋጀዋለን።
11. ገሀነም በወደቀ ጊዜ ያ! ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመዉም።
12. ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን።
13. መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛው ነው።
14. የምትንቀለቀል እሳት አስጠነቀቅኳችሁ።
15. ከጠማማ በስተቀር የማይገባባትን
16. ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝም የሸሸ እድለ ቢስ (ነው የሚገባባት)።
17. አላህን በጣም ፈሪ የሆነ በእርግጥ ይርቃታል::
18. ያ (ከወንጀል) የሚጥራራ ሲሆን ገንዘቡን የሚለግስ፤
19. ለአንድም ሰው በእርሱ ዘንድ ተመላሽ የሚሆን ውለታ ሳይኖርበት።
20. የታላቁን ጌታውን የአላህን ውዴታ በመፈለግ ብቻ (ይህንን የሰራ) ሲቀር።
21. እርሱማ ወደ ፊት (በሚሰጠው) በእርግጥ ይደሰታል።