The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe morning hours [Ad-Dhuha] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The morning hours [Ad-Dhuha] Ayah 11 Location Maccah Number 93
በረፋዱም፤ (እምላለሁ)
2. በሌሊትም ጸጥ ባለ ጊዜ እምላለሁ::
3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም::
የመጨረሻይቱ ዓለም ከመጀመሪያይቱም ይልቅ ላንተ በላጭ ናት::
ጌታህም ወደ ፊት ብዙ ስጦታ በእርግጥ ይሰጥሃል። ትደሰታለህም።
6. የቲም ሆነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)::
7. የሳትክም ሆነህ አገኘህና መራህ::
8. ደሃም ሆነህ አገኘህና አከበረህ::
9. እናም የቲምን አትጨቁን::
10. ለማኝንም አትገላምጥ::
11. የጌታህንም ጸጋ ግለጽ::