The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Fig [At-Tin] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The Fig [At-Tin] Ayah 8 Location Maccah Number 95
1. በበለስና፤ በወይራ ዛፍ እምላለሁ፣
2. በሲና ተራራም፤
3. በዚህ በጸጥተኛው (ጸጥታ በነገሰበት) አገር መካም እምላለሁ።
4. በርግጥ ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው::
5. ከዚያም (ከፊሉን) ከበታቾች ሁሉ በታች አድርገን መለስነው::
6. እነዚያ በአላህ ያመኑትና መልካም ተግባራት የሰሩት ሲቀሩ ለእነርሱማ የማይቋረጥ ምንዳ አለላቸው::
7. (የሰው ልጅ ሆይ) ታዲያ ከዚህ (እውነታ) በኋላ በፍርዱ ምን አስተባባይ አደረገህ?
8. አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን?