عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The Clot [Al-Alaq] - Amharic translation - Africa Academy

Surah The Clot [Al-Alaq] Ayah 19 Location Maccah Number 96

1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚያ (ሁሉንም ነገር) በፈጠረ ጌታህ ስም (ጀምርና) አንብብ! {1}

2. ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)::

3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንብብ! ጌታህም በጣም ቸር ነው::

4. ያ በብዕር ያስተማረ (ጌታ)፤

5. የሰውን ልጅ ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ (ጌታ)::

6. በእውነቱ የሰው ልጅ ወሰንን ያልፋል::

7. ራሱን የተብቃቃ ሆኖ በማየቱ ምክንያት

8. መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው::

9. ያንን የሚከለክለውን አየህን?

10. ባሪያን በሰገደ ጊዜ (የሚከለክለውን):

11. እስቲ ንገረኝ (ተከልካዩ ባሪያየ) በትክክል መንገድ ላይ ቢሆን፤

12. ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ ምን እንደሚሆን አየህን?

13. እስቲ ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና ከእምነት ቢሸሽ፤

14. አላህ የሚያይ መሆኑን አያውቅምን?

15. ይታቀብ፤ የማይከለከል ከሆነ አናቱን ይዘን አንጎትተዋለን::

16. ያቺን ውሸታምና ስህተተኛ የሆነችውን አናቱን::

17. ሸንጎውንም ይጥራ፤

18. እኛም ዘበኞቻችንን እንጠራለን::

19. በጭራሽ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህን ለሚል ከሓዲ አትታዘዘው፤ ስገድ፤ ወደ አላህም ተቃረብ። {1}