عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The Clear proof [Al-Bayyina] - Amharic translation - Africa Academy

Surah The Clear proof [Al-Bayyina] Ayah 8 Location Madanah Number 98

1. ከመጽሐፍ ባለቤቶችና ከአጋሪዎች እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች ግልጽ አስረጂ እስኪመጣላቸው ድረስ (ከነበሩበት አቋም) ተወጋጆች አልነበሩም::

2. (አስረጂውም) የተጥራሩ (መጽሐፎችን) የሚያነብ ከአላህ የሆነ መልዕክተኛ ነው።

3. በውስጧም ቀጥተኛ የሆኑ ጹሁፎች ያሉባት የሆነችን (አስረጂ)፤

4. እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡ ሰዎችም ግልጽ አስረጂ ከመጣላቸው በኋላ እንጂ አልተለያዩም::

5. ሃይማኖትን ለአላህ ብቻ አጥሪዎችና ቀጥተኞች ሆነው አላህን ሊገዙት፤ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ፤ ዘካንም በትክክል ሊሰጡ እንጂ ያልታዘዙ ሲሆን ተለያዩ:: የቀጥተኛይቱ ሃይማኖት ድንጋጌም ይሀው ነው።

6. ከመጽሐፉ ባለቤቶችና ከአጋሪዎች እነዚያ የካዱት በውስጧ ዘውታሪዎች በሚሆኑባት የገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው:: እነዚያ ከፍጥረቱ ሁሉ መጥፎዎቹ እነርሱ ናቸው::

7. እነዚያ በትክክል አምነው በጎ ተግባራትንም የሰሩት እነዚያ ከፍጥረት ሁሉ በላጭ (ምርጦች) የሆኑት እነርሱ ናቸው።

8. ምንዳቸውም በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ከጌታቸው ዘንድ የሚቸሯቸው የመኖሪያ ገነቶች ናቸው። በውስጣቸው ለዘልዓለም ዘወታሪዎች ሲሆኑ ይገቡባቸዋል:: አላህ ከእነርሱ ስራቸውን ወደደላቸው:: እነርሱም ከእርሱ ምንዳውን ወደዱ:: ይህ እድል ጌታውን ለፈራ ሁሉ ነው::