The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe earthquake [Al-Zalzala] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The earthquake [Al-Zalzala] Ayah 8 Location Madanah Number 99
1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምድር በኃይል መንቀጥቀጧን በተንቀጠቀች ጊዜ፤
2. ምድርም ሸክሞቿን ባወጣች ጊዜ፤
3. ሰዉም "ምን ሆነች?" ባለ ጊዜ፤
4. በዚያ ቀን ወሬዎቿን ትናገራለች::
5. ጌታህ ለእርሷ አሳውቋታልና፤
6. በዚያ ቀን ሰዎች ሁሉ ስራዎቻቸውን እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ እንደየስራቸው የተበታተኑ ሆነው ከየመቃብራቸው ወደ መቆሚያው ስፍራ ይመለሳሉ::
7. የብናኝን ክብደት ያህል መልካም የሰራ ሰው ያገኘዋል::
8. የብናኝን ክብደት ያህል ክፋት የሰራ ሰውም ያገኘዋል::